/ categories / News / @dw_amharic / post #6146
1682

ዋና ዋና ዜናዎቹ
የኢትዮጵያ፣ የሱዳን እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የምትገነባውን ግድብ አስመልክቶ የገቡበትን ውዝግብ ለመፍታት እንደሚሠሩ አመለከቱ። የሦስቱ ሃገራት የውኃ ሚኒስትሮች በቀጣይ አራት ስብሰባዎችን ዋሽንግተን ላይ እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።

የሲዳማ ብሄር ለሚያካሂደው ህዝበ ውሳኔ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል። ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ እስከ ኅዳር 6 ቀን 2012 ዓ,ም ድረስ ይዘልቃል።

በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ራሳቸውን «ቄሮ» በሚል ስም አደራጅተው በጀርመን የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያውያንን ስብሰባ በኃይል ለማወክ ሞክረዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተ።ለኢትዮጵያውያን ሁሉ በተጠራው ስብሰባ እንዳንሳተፍ አድሎ ተፈፅሞብናል ያሉት እነዚህ ወገኖች በበኩላቸው ክሱን በሕግ እንደሚከራከሩ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

የተመድ በፀጥታው ምክር ቤት የደቡብ ሱዳን ተቃናቃኝ ኃይሎች ከአንድ ዓመት በፊት የተፈራረሙትን የሰላም ውል እንዲያከብሩ አሳሰበ።
https://p.dw.com/p/3SeO7?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot


17:05 07.11.19
@dw_amharic
24.09K +332

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።